ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉን ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በመወከል አቶ ያዕቁብ ፈቂ፤ ለጎፋ ዞን ዋና አሰተዳደሪ ዳግማዊ አየለ (ኢ/ር) አስረክበዋል፡፡ ከድጋፉ ውስጥ 10 ሚሊየን ብር ለተጎጂዎች አፋጣኝ እርዳታ፣ 15 ሚሊየን ብር ደግሞ አካባቢውን በዘላቂነት ለማልማት የሚውል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፤ ተጎጂዎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለው ድጋፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በዞኑ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማውን ሐዘን በድጋሚ ገልጾ ለተጎጂዎች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
EBC
More Stories
የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)