አገለግልቶቹ ከውጭ ሀገር በቀላሉ ገንዘብ ለመላክና ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን መፈጸም የሚያስችሉ ናቸውኢትዮ ቴሌኮም በትናንትናው እለት ቨርችዋል ቪዛ ካርድ፣ ቪዛ ዳይሬክትና ቴሌብር ሬሚት የተሰኙ አገልግሎቶችን ማስጀምሩን አስታውቋል።የቴሌ ብር ደምበኞች ከውጭ ሀገራት ገንዘብ ለመቀበል የሚያስችል የቪዛ ዳይሬክት እና ቴሌብር ሬሚት አገልግሎቶች ለማቅረብ የሚያስችል የአጋርነት ስምምነት ከቪዛ ኩባንያ ጋርም ተፈራርሟል።በስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ፤ ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ ያስጀመራቸው አገልግሎቶች ነባሩን ሐዋላ አግልግሎቶችን “በእጅጉ የሚያዘምን” መሆኑን ገልጸዋል። መተግበሪያቸውን ማዘመን የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ወደ ቴሌብር መተግበሪያቸው በመግባት ከሚመጣላቸው ዝርዝር ውስጥ ቪዛ የሚለውን በመምረጥ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።ከዚያ በኋላም ባለ16 አሀዝ የቨርችዋል ቪዛ ካርድ ቁጥር የሚደርሳቸው ሲሆን፤ ይህም ለደንበኛው የሚደርስ ልዩ እና ብቸኛው የተጠቃሚው መለያ ቁጥር መሆኑን ነው ኢትዮ ቴሌኮም ያስወቀው።ቪዛ ዳይሬክት ምንድን ነው፤ እንዴትስ መጠቀም እንችላለን?የቪዛ ዳይሬክት አገልግሎት በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚኖሩ የቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች የቴሌብር ቨርቹዋል ቪዛ ካርድ ቁጥርን ብቻ በመጠቀም ገንዘብ ወደ ሀገር ቤት ለማስተላለፍ የሚያስችል ነው።ይህ የቪዛ ዳይሬክት አገልግሎት ግለሰቦችም ሆነ ተቋማት ገንዘብ ከ190 ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ በቀላሉ ለመላክ የሚያስችል ነው።ደንበኞች በቪዛ ዳይሬክት ገንዘብ ለመቀበል በቅድሚያ በቴሌብር ሱፐርአፕ ቨርችዋል ቪዛ አገልግሎት መመዝገብ የሚጠበቅበባቸው ሲሆን፤ ከዚያም ባለ16 አሀዝ የቨርችዋል ቪዛ ካርድ ቁጥር ለላኪው ማጋራት ብቻ በቀላሉ ገንዘብ ማስላክና መቀበል ይችላሉ።የቴሌብር ሬሚት አገልግሎትስ ምንድነው? እንዴትስ እንጠቀማለን?የቴሌብር ሬሚት አገልግሎት በኢትዮ ቴሌኮም በውስጥ አቅም የተሰራ መተግሪያ ሲሆን፤ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ተጠቃሚዎች የቴሌብር ሬሚት መተገበሪያውን በስልካቸው ላይ ብቻ በመጫን በሞባይል ስልክ ቁጥራው በቀላሉ ገንዘብ ለመላክ የሚያስችል ነው።መተግበሪያ ለጊዜው በ9 የውጪ ሀገራት ያሉ ደምበኞች ወደ ሀገር ቤት ገንዘብ መላክ የሚችሉበት መሆኑንም የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ አስታውቀዋል።በአገልግሎቱ ደንበኞች የቴሌብር ሞባይል ቁጥራቸውን ብቻ በማጋራት ከአሜሪካ፣ ካናዳ፣ እስራኤል፣ ሳኡዲአረቢያ፣ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጣሊያን እና ስዊድን ገንዘብ በሃዋላ መቀበል የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
Al-Ain
More Stories
የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ ያደርጋል
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ