January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ አንድ እመርታ የታየበት ደረጃ ላይ ደርሰናል- ጠ/ሚ ዐቢይ ( ዶ/ር)

በዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ አንድ እመርታ የታየበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ኢትዮ ቴሌኮም ከቪዛ ኩባንያ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን በኪስ የሚያዝ ቨርቱዋል ቪዛ ካርድ ብሎም የተሻሻለ የሃዋላ አገልግሎት በቪዛ ዳይሬክት እና በቴሌብር ረሚት አቅርቧል ብለዋል።ቪዛ ዳይሬክት ከ190 ሀገራት በላይ ቀለል ያለ የገንዘብ ማዘዋወር አገልግሎትን በቴሌብር ቨርቱዋል ካርድ ቁጥር አማካኝነት የሚያቀላጥፍ አንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡ይህ አዲስ አገልግሎት ከ47 ነጥብ 55 ሚሊየን በላይ የሆኑ የቴሌብር ተጠቃሚዎችን እንደሚያገለግል ጠቁመው÷ በዚህም ኢትዮ ቴሌኮም ትልቅ ሥራ ሰርቷል ሲሉ አውስተዋል፡፡

FBC