January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ከነዳጅ አውቶሞቢሎች እና የፀጥታና ደህንነት ዕቃዎች ውጪ ሌሎች ዕቃዎች ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ወደ ሀገር እንዲገቡ ተፈቀደ

የገንዘብ ሚኒስቴር ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ዕቃዎችን ወደ ሀገር ማስገባትን በተመለከተ ለጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሰርኩላር አስተላልፏል።በዚህም ወደ ሀገር እንዳይገቡ በሕግ ክልከላ ከተደረገባቸው የነዳጅ አውቶሞቢሎች እና የፀጥታና ደህንነት ዕቃዎች ውጪ ሌሎች ዕቃዎች ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ወደ ሀገር እንዲገቡ በመንግሥት የተወሰነ መሆኑን በመግለጽ ይኸው ተግባራዊ እንዲደረግ አሳስቧል።መንግሥት በቅርቡ ተግባራዊ ባደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ፤ የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያው አማካኝነት እንዲወሰን ማድረጉ እና ይኸው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል።

EBC