January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

“አዲሱ ስርዓተ ትምህርት አንድ ተማሪ 3 ቋንቋዎችን እንዲናገር የሚያስችል ነው” – ትምህርት ሚኒስቴር

ከትምህርት ሚኒስቴር ዓበይት የሪፎርም ትኩረቶች አንዱ የስርዓተ ትምህርት ሪፎርም ነው።አዲሱ ስርዓተ ትምህርት አንድ ተማሪ 3 ቋንቋዎችን እንዲናገር የሚያስችል መሆኑን በሚኒስቴሩ የተፈጥሮ ሳይንስ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ኃላፊ ዛፏ አብርሃ ለኢቢሲ ገልፀዋል።ተማሪዎች በቅድመ አንደኛ ደረጃ በአፍ መፍቻ ቋንቋ፣ በአንደኛ ደረጃ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ማለትም እንግሊዝኛ ከዚያም ከ3ኛ ክፍል በኋላ ሌላ የአጎራባች ክልል ቋንቋ እንደሚማሩ ኃላፊዋ አስረድተዋል።የአጎራባች ክልል ቋንቋውም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሳይሆን በክልሎች የሚመረጥ እንደሆነም ነው የገለፁት።

EBC