October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ክልላዊ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ዉጤት ይፋ ሆነ

በ2016 የትምህርት ዘመን ክልላዊ 8ኛ ክፍል ፈተና ከተፈኑ ተማሪዎች 42.93 ከመቶ ተማሪዎች ከ50 % በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ ።በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ እንዳስታወቁት በክልሉ በ2016 የትምህርት ዘመን 42.93 ከመቶ ተማሪዎች ከ50% በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ተናግረዋል ።በክልሉ በ2016 ዓ.ም 21 ሺህ 428 ወንዶች እና 23 ሺህ 658 ሴቶች በድምሩ 45 ሺህ 86 ተማሪዎች ፈተና ላይ መቀመጣቸውን አቶ አልማው ገልፀዋል ።ክልል አቀፍ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከተፈተኑት 45 ሺህ 86 ተማሪዎች መካከል ወንድ 9 ሺህ 836 ሴት 9 ሺህ 519 በድምሩ 19 ሺህ 355 ተማሪዎች ከ50 % በላይ ውጤት አቶ አልማው ተናግረዋል።እንደ ኃላፊዉ ገለጻ በፈተናዉም ከ ዳዉሮ ዞን ኤምቲ የአንደኛና መካካለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ተስፋለም ታምራት አማካይ ነጥብ 94.17 ፐርሰንታይል 100 እና አጠቃላይ ዉጤት 659 በማምጣት ከፍተኛ ዉጤት ሆኖ ተመዝግቧል ብለዋል።በ2016 የትምህርት ዘመን ከትምህርት ቤት እስከ ክልል ኩረጃን ለማስቀረት በተሰራው ቅንጅታዊ ስራ ተማሪዎች የራሳቸውን ውጤት በጥረት ማምጣታቸዉን ተናግረዉ ለዚህም ስኬት ተባባሪ ለሆኑት አካላት በክልሉ ትምህርት ቢሮ ስም አቶ አልማው ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።ተማሪዎች በgoogle account sw.ministry ብለው በመግባት view result የሚለውን በመጫን መመዝገቢያ ቁጥራቸውንና ስማቸውን በማስገባት ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማወቅ እንደሚችሉ የቢሮ ኃላፊዉ አስታውቀዋል ። የዘገበው የክልሉ መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው ።