የአስተዳደር ቢሮዎች መቀመጫ የሚሆነው አዲስ ዋና ከተማ በ617 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል ተብሏልምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ታንዛኒያ በ5 ቢሊየን ዶላር አዲስ ዋና ከተማ እያስገነባች መሆኑ ተሰምቷል፡፡በ2021 በስልጣን ላይ እያሉ ህይወታቸው ባለፈው የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ስም ይሰየማል የተባለው አዲስ ዋና ከተማ የዲፕሎማቲክ እና የአስተዳደር ቢሮዎች መቀመጫ እንደሚሆን ተገልጿል።617 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው አዲሱ ከተማ ከአሁኗ የሀገሪቱ ዋና ከተማ ዶዶማ በ17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገነባ ነው፡፡በአሁኑ ወቅት የሚንስቴር መስርያ ቤቶች እና የአስተዳደር ቢሮዎች ግንባታ የተጀመረ ሲሆን ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ በዋና ከተማዋ የሚገኙ የፕሬዝዳንቷን ቢሮ ጨምሮ ሌሎች የአስተዳደር ቢሮዎች ሙሉ ለሙሉ ወደ አዲሱ ከተማ እንደሚዘዋወሩ ተሰምቷል፡፡የታንዛኒያ መንግስት የአስተዳደር ቢሮዎችን በአንድ ስፍራ መሰብሰብ የቢሮክራሲ አሰራሮችን እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ያግዛል ብሏል፡፡የሀገሪቱ የቤቶች ኮርፖሬሽን ከተማውን በዋናነት በሃላፉነት ተቀብሎ እያስገነባ የሚገኝ ተቋም ነው።
Al-Ain
More Stories
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ
አስደንጋጩ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት አልበረደም