January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያዩ

በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋም ተገኝተዋል። የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ መንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል። ውይይቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት አባላት ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር መስተጋብር እንዲፈጥሩ ያስቻለ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

EBC