January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የተሳተፉ ዜጎች የትልቅ ታሪክ አካል ናቸው – ቢልለኔ ስዩም

በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የሚከናወኑ ተግባራት ለቀጣይ ትውልድ የሚተርፉ ሥራዎች መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽኅፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገለጹ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ ተከትሎ በፓሪስ ኦሎምፒክ የድል ባለቤት የሆኑ አትሌቶችን ጨምሮ አርቲስቶች፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዛሬ ችግኝ ተክለዋል። በመርኃ ግብሩ ተሳታፊዎች መካከል ችግኝ በፍጥነት የመትከል ውድድሮችና ሌሎችም ሁነቶች ተከናውነዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽኅፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም እንደገለፁት፤ አረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋ ሥጋትን ከመከላከል አንጻር የማይተካ ሚና ይጫወታል። የአረንጓዴ አሻራ ተግባራት የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባሻገርም ጽዱ፣ ውብና ጤናማ አካባቢን ለትውልድ ለማስተላለፍ

EBC