የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ተወካዩን ቢልክም የሱዳን ጦር ባለመሳተፉ ፊት ለፊት ድርድር መጀመር አልቻሉም
አሜሪካ እና ሳኡዲ ባዘጋጁት የጄኔቫው የሰላም መድረክ ኤምሬትስና ግብፅ እየተሳተፉ ነውየሱዳን ተፋላሚ ጀነራሎችን ለማቀራረብ ያለመ ምክክር በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ተጀምሯል።በአሜሪካና ሳኡዲ መሪነት እየተካሄደ ባለው መድረክ ግን ዋነኛ ተፋላሚዎቹ አልተገናኙም።የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ (አርኤስኤፍ) ተወካዩን ወደ ጄኔቫ ቢልክም በጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሀን የሚመራው የሱዳን ጦር ግን በድርድሩ አልሳተፍም ብሏል።በዚህም ምክንያት ሁለቱን ተፋላሚ ሀይሎች ፊት ለፊት ለማገናኘት የተያዘው እቅድ ሳይሳካ መቅረቱን በሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሬሎ ተናግረዋል።
Al-Ain
More Stories
ሩሲያ በዩክሬን የኢነርጂ መሰረተ ልማት ተቋማት ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ለማቆም ተስማማች
አሜሪካ በየመን የሀውቲ ታጣቂዎች ላይ አዲስ የአየር ጥቃት መፈጸሟ ተገለጸ
ትራምፕ “የወንበዴ” ቡድን አባላት ናቸው ያሏቸውን ከ200 በላይ ቬንዙዌላውያን ከአሜሪካ አባረሩ