November 21, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል። የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር 3ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው ለርዕሰ መስተዳድሯ ሹመቱን የሰጠው፡፡ አዲስ ሹመት የተከናወነው ወቅቱ የሚጠይቀውን አሻጋሪ የለውጥ አመራር በማምጣት የህዝቡ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ፍላጎቶች በተገቢው መንገድ ምላሽ እንዲያገኙ ለማስቻል እንዲሁም የቀድሞው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በገዥው ፓርቲ ለሌላ ተልዕኮ በመፈለጋቸው መሆኑም ተጠቅሷል። ወይዘሮ ዓለሚቱ አሞድ ቀደም ሲል የክልሉ ምክትል አፈ- ጉባኤ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆንና በሌሎች የተለያዩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊነቶች ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተጠቁሟል፡፡ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ በክልሉ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ መስተዳድር መሆናቸውም ተገልጿል። በሚፍታህ አብዱልቃድር

EBC

You may have missed