January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአንካራ በተካሄደው ድርድር ኢትዮጵያ የባሕር በር እንደሚያስፈልጋት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲረዳ ማድረግ ተችሏል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

በአንካራ በተካሄደው ድርድር ኢትዮጵያ የባሕር በር እንደሚያስፈልጋት የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የተረዳበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ መንግስት ሰላማዊ እና ህጋዊ በሆነ መንገድ የባሕር በር በጋራ የማልማት እና የመጠቀም እንቅስቃሴውን እንደሚገፋበት ተነግሯል፡፡ ይህ የተገለፀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ነው፡፡ በሳምንታዊ መግለጫውም በቱርክ አንካራ በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የተደረገው ሁለተኛው ዙር የሁለትዮሽ ድርድር ተስፋ ሰጭ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

EBC