የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አህመድ ሺዴ በጂቡቲ የኢነርጂ ሚኒስትር ሚ/ር ዮኒስ አሊ ገዲ ከተመራ የሀገሪቱ ልኡካን ቡድን ጋር በሼራተን አዲስ ሆቴል ተወያይተዋል።ውይይቱ በተለይ በጂቡቲ የሚገኘው ሆራይዘን ተርሚናል ለኢትዮጵያ ነዳጅ የመጫን አገልግሎትን በሚያጠናክርበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር።በዚህም ሆራይዘን ተርሚናል ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን አገልግሎት እንዲያቀላጥፍ፤ አልፎ አልፎ በነዳጅ ስርጭቱ ላይ የሚፈጠረው መቆራረጥ እንዳይከሰት እና ምንም ክፍተት እንዳይኖር ለማድረግ ያለመ ውይይት መካሄዱን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።ከዚሁ ጋር በተያያዘም አዋሽ ዴፖን ከጂቡቲ ሆራይዘን ተርሚናል ጋር በባቡር ለማገናኘት እየተደረገ ባለው ጥረት ተጓተው የቆዩ ስምምነቶች በአስቸኳይ በሁለቱም ወገኖች በተሰየሙ የቴክኒክ ኮሚቴዎች ታይተው ወደ ሙሉ ስምምነት በመድረስ በመጪው መስከረም ወር 2017 ዓ.ም ውሉ ተፈርሞ የፕሮጀክቱ ግንባታ እንዲጀመር ከስምምነት ተደርሷል።በውይይቱ የሆራይዘን ተርሚናልና የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የስራ ኃላፊዎች፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ተገኝተዋል።
EBC
More Stories
የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)