November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ተካሄደ

የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የማስጀመሪያ መርሐ- ግብር ተካሂዷል፡፡በ35 ሄክታር መሬት ላይ ከቻይናው “ሲሲሲሲ” ጋር በመተባበር የሚገነባው ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በከተማ ውስጥ አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል ግዙፍ ፕሮጀክትመሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡የኢኮኖሚ ዞኑ በውስጡ ትላልቅ ሞሎችን፣ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን፣ ቢሮዎችን፣ የትምህርት እና የጤና ተቋማትን እንዲሁም ሰፋፊ መዝናኛዎችንና የውሃ አካላትን እንዲሁም የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላትን ያካተተ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡አዲሱ የኢኮኖሚ ዞን ለመዲናዋ አዲስ ገፅታ የሚያላብስ፣ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያጎላ፣ ተጨማሪ የውበት ምንጭ የሚሆን፣ ለነዋሪዎች ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር እና ንግድን የሚያሳልጥ ትልቅ ዓለም አቀፍ የግብይት ማዕከል ይሆናል ብለዋል፡፡በተጨማሪም ኢኮኖሚ ዞኑ ማህበራዊ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶችን ያካተተ ሲሆን ፥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ ስራ እንደሚገባ ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል፡፡

FBC