January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያና ሶማሊያ ሁለተኛውን ዙር ውይይት አደረጉ

ኢትዮጵያና ሶማሊያ ሁለተኛውን ዙር ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አስታውቀዋል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷በቱርክ አመቻችነት በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል 2ኛ ዙር ዉይይት በአንካራ መካሄዱን ገልጸዋል።አምባሳደር ታዬ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃከን ፊዳን ከውይይቱ በፊት ኢትዮጵያን በመጎብኘታቸው ምስጋና አቅርበዋል።“የኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ያላት ህጋዊ ፍላጎትም በሰላማዊ መንገድ ከጎረቤቶቻችን ጋር በመተባበር እንደሚፈፀም እርግጠኛ ነኝ” ሲሉም ገልጸዋል።

FBC