የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመቋቋም የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ጥረቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ሚናዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተመላከተ፡፡የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ዕድገት ኢንስቲትዩት፣ ከግብርና ሚኒስቴር እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፥ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብሩ የሀገሪቱን የደን ሽፋን በ2011 ዓ.ም ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ ዘንድሮ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ አሳድጎታል ብለዋል፡፡አረንጓዴ ዐሻራ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ስለሆነ አጠናክሮ ለማስቀጠል ይሠራል ማታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡መርሐ-ግብሩ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው የውኃ አካላት መጎልበት ዘርፈ ብዙ ሚና እንዳለው ገልጸው÷ በአረንጓዴ ዐሻራ ዙሪያ ያላትን ልምድ ለጎረቤት ሀገራት በማካፈል ሚናዋን እየተወጣች ነው ብለዋል።ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚደረጉ ጥረቶች ላይ ሚናዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።የዓለም አቀፉ አረንጓዴ ዕድገት ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ቢሮ ዳይሬክተር ኦኬቹኩ ዳንኤል ኦግቦናያ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ ላይ እያከናወነች ያለው ተግባር ምሳሌ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን የሚቋቋም የግብርና ስርዓትን ለመገንባት በኢትዮጵያ የተጀመሩ ስራዎች አበረታች ውጤት እየተመዘገበባቸው መሆኑንም ገልጸዋል።ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ ጋር በአረንጓዴ ልማት የጀመረውን የትብብር ስራ እንደሚያስቀጥልም ጠቁመዋል።
FBC
More Stories
የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ተገለጸ፡፡
የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተመረጡ የግብርና፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ እና ማዕድን ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበየቻይናዋ ግዛት ከፍተኛ ልዑካን የተሳተፉበት የቻይና-አፍሪካ (ኢትዮጵያ) የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝም ና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም ለ45ኛ በኢትዮጵያ ለ37ኛ በክልሉ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የዓለም የቱሪዝም ቀን ”ቱሪዝም ለሰላም” በሚል መር ቃል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነዉ።