November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በጋምቤላ ክልል የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ፕሬዚዳንት አክሊሉ ታደሰ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የአባላቱን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ።

ሊጉ አባላቱን በማስተባበር ባለፈው ዓመት በመላ ሀገሪቱ ከ460 ሚሊየን በላይ ችግኝ መትከሉን አስታውሰዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አባላት እንዳለው ጠቁመው÷በዘንድሮው ዓመት 500 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የሊጉ አባላት በበኩላቸው÷የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አንድነትን በማጠናከር ሁለተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያግዛል ብለዋል።

በተያዘው ክረምት በመላ ሀገሪቱ አባላትን በማስተባበር ችግኞችን በመትከል የአረጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን የመደገፍ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል።

የተራቆቱ አከባቢዎች በደን ለመሸፈን እየተደረገ ባለው ጥረት ችግኞችን በየጊዜው መንከባከብ እንደሚያስፈልግ መጠቆማቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

FBC