January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በጋምቤላ ክልል በጎርፍ ምክንያት 16 ሺህ ወገኖች በጊዜያዊ መጠለያ እንዲሰፍሩ ተደረገ

 በደጋማው አካባቢ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በጎግ፣ በላሬ፣ በጆር እና በዋንቱዋ ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ መከሰቱን የጋምቤላ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር አስታወቀ፡፡

በተከሰተው የጎርፍ አደጋም ከ16 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን እና ለጊዜው ደረቃማ በሆኑ አካባቢዎች እንዲሰፍሩ መደረጉ ተጠቅሷል፡፡

ከክልሉ መንግሥትና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመነጋገር ለተፈናቃዮቹ አፋጣኝ ድጋፍ የሚደርስበት ሁኔታ እንደሚመቻችም ተጠቁሟል፡፡

የጎርፍ አደጋው በቤት ውስጥ ያሉ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በቁም እንስሳትና ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

FBC