October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ በኦሊምፒኩ የመጀመሪያ ወርቋን አገኘች

በፓሪስ 2024 የኦሊምፒክ ወድድር በማራቶን ኢትዮጵያ በአትሌት ታምራት ቶላ አማካኝነት የመጀመሪያ ወርቋን አግኝታለች፡፡

በፓሪስ ኦሊምፒክ የወንዶች የማራቶች ውድድር የተካሄደ ሲሆን ÷አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ ታምራት ቶላና ደሬሳ ገሌታ ኢትዮጵያን ወክለው ተወዳድረዋል።

በዚህም ታምራት ቶላ ውድድሩን 2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ በመግባት በቀዳሚነት በማጠናቀቅ በኦሊምፒኩ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡

አትሌት ደሬሳ ገለታ ደግሞ ውድድሩን በአምስተኛ ደረጃ አጠናቋል፡፡