November 21, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አሜሪካ የኢራን መረጃ መንታፊዎችን ለጠቆመኝ 10 ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ አለች

ሳይበር አቬንጀርን የሚል ስያሜ ያላቸው ኢራናዊያን የእስራኤል እና አሜሪካ ተቋማትን ኢላማ አድርገዋል

የቡድኑ አባላት የኢራን አብዮት ጠባቂ ጦር ስር የተዋቀሩ ናቸው ተብሏል

አሜሪካ የኢራን መረጃ መንታፊዎችን ለጠቆመኝ 10 ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ አለች፡፡

የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ እንዳስታወቀው በተደጋጋሚ በተቋማት ላይ የበይነ መረብ ጥቃት በሚያደርሱ የኢራን ሳይበር ቡድን ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል፡፡

ቢሮው አክሎም እነዚህ መሰረታቸውን ኢራን ያደረጉ የሳይበር ጥቃት ቡድን ያሉበትን ለጠቆመ 10 ሚሊዮን ዶላር በወሮታ መልኩ እከፍላለሁ ብሏል፡፡

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ይህ የመረጃ መንታፊዎች ቡድን በኢራን አብዮት ጥበቃ ጦር ስር የተደራጀ ሲሆን የአሜሪካ እና እስራኤል ተቋማትን በማጥቃት ይታወቃል፡፡

እስካሁን ባደረሳቸው የበይነ መረብ ጥቃቶችም ተቋማት መደበኛ ስራቸውን እንዳይሰሩ ማስተጓጎልን ጨምሮ ጥብቅ መረጃዎችን ሲመነትፍ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

ስድስት አባላት ያሉት ይህ አደገኛ የመረጃ መንታፊዎች ቡድን በተለይም የእስራኤል እና አሜሪካ የሎጅስትክ ተቋማትን ኢላማ ሲያደርግ እንደነበር በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

AL AIN

You may have missed