October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአዲስ አበባ እየተመዘገበ የመጣው ሁለንተናዊ ለውጥ እያደገ ካለው የገቢ አሰባሰብ ሥርዓት የሚመነጭ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ


ከከተማ እስከ ወረዳ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮችን ያሳተፈ የ2016 አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 ዕቅድ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መድረኩን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት፥ በአዲስ አበባ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመዘገብ ካስቻሉ በርካታ ጉዳዮች መካከል ገቢ ከማሳደግ አንጻር የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ወሳኝ ሚና አላቸው።

ገቢ ለአንድ ሀገር ብልፅግና የጀርባ አጥንት ነው ያሉት ከንቲባዋ፣ በበጀት ዓመቱ 146.84 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ጠቅሰው፣ ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ44.16 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች በ2017 አዲስ አበባ ከምታመነጨው ኢኮኖሚ በተገቢው መጠን ገቢ በማሰባሰብ የተጀመረውን ሁለንተናዊ ለውጥ ማሳለጥ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

EBC