January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በሀረሪ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ተጀመረ


በሀረሪ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በይፋ ተጀምሯል።

ክልላዊ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፉ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 6 ቀናት የሚቆይ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ተገኘወርቅ ጌጡ የምክክር ሂደቱ ለኢትዮጵያ ተስፋን በማለምለም ችግሮችን ከግጭት ይልቅ በውይይት የመፍታት ባህል የሚጎለብትበት እንደሆነ ገልፀዋል።

በመድረኩ የተለያዩ የማህበረሰብ ወኪሎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሶስቱ የመንግሥት አካላት ወኪሎች፣ የተለያዩ ማህበራት እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እየተሳተፉ ነው።

በአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረኩ ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ሀሳቦችና አጀንዳዎች ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

EBC