October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በድሬዳዋ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ አጀንዳ ማሰባሰብ ይጀምራል

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በድሬዳዋ አስተዳደር ከነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ አጀንዳ ማሰባሰብ እንደሚጀምር አስታወቀ።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር አምባሳደር መሐመድ ድሪር በሰጡት መግለጫ÷ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም በከተማው ከሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮች አስመርጦ ማዘጋጀቱን አስታውሰዋል፡፡

በመሆኑም ኮሚሽኑ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር በሚያከናውነው የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ የማህበረሰብ ወኪሎች፣ የመንግስት አካላት፣ ፓርቲዎች የተለያዩ ተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም ታዋቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ይመክራሉ፡፡

በዚህ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ 1 ሺህ የሚደርሱ ዜጎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

አጀንዳ ማሰባሰቡ ከሰኞ ጀምሮ ለስድስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን÷ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ በንቃት እንዲሳተፋ መልዕክት ተላልፏል።

ምክክሩ መሰረታዊ የሆኑና አንኳር ጉዳዮችን ለመለየት እንደሚያግዝም ተመላክቷል፡፡

FBC