January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ዩክሬን ሩሲያ ውስጥ ዘልቃ በመግባት የአየር ጦር ሰፈር መደብደቧን ገለጸች

የሩሲያ ሱ-34፣ ሱ-35 እና ሚግ-31 አውሮፕላኖች በዚህ የአየር ጦር ሰፈር እንደነበሩ የዩክሬን ጦር ገልጿልዩክሬን ሩሲያ ውስጥ ዘልቃ በመግባት የአየር ጦር ሰፈር መደብደቧን ገለጸች።የዩክሬን ጦር በምዕራብ ሩሲያ በሊፕስክ ግዛት በሚገኘው የአየር ጦር ሰፈር ላይ ሌሊቱን ባደረሰው ድብደባ ቦምቦችን ማውደሙን እና በርካታ ፍንዳታዎችን ማድረሱን ገልጿል።ኪቭ በሩሲያ የአየር ኃይል ሰፈሮች ላይ ጥቃት እያደረሰች ያለችው፣ ሩሲያ የጦር አውሮፕላኖቿን ተጠቅማ የምታደርሰውን የማጥቃት አቅም ለማዳከም ነው።

Al Ain