የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ሚና የሚያሳድግ ነው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ አስገነዘቡ፡፡የ2016 በጀት ዓመት የግብር አሰባሰብ ዕቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡በመድረኩ አቶ አህመድ ሽዴ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ለግብር ከፋዮች በሰጡት ማብራሪያ፤ መንግስት እየሰበሰበ ያለው ገቢ ከሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ነው ብለዋል።የኢኮኖሚ ማሻሻያው የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ሚና የሚያሳድግ ነው ሲሉም ነው የገለጹት፡፡ማሻሻያው ለሀገር ውስጥ አምራቾች ቅድሚያ ይሰጣል በማለት ገልጸው÷ በብድር ረገድ በተለይ መንግስት ከዚህ በፊት በስፋት ይወስደው የነበረውን ብድር በማስቀረት የተሻለ የብድር ፍሰት ለግሉ ዘርፍ እንደሚኖር አንስተዋል፡፡መንግስት የገቢ አቅሙን ለማሳደግ የሚያስችለውን ስራ ግብረ ሃይል በማቋቋም ጭምር በከፍተኛ ትኩረት እየሰራ ነውም ብለዋል፡፡በበጀት ዓመቱ ዕቅድ አስቀድሞ ከተቀመጠው በተጨማሪ ከሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት አንድ በመቶ ተጨማሪ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱንም ጠቁመዋል።የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው÷ ባለፉት አምስት ዓመታት ገቢ በሶስት እጥፍ ማደጉን ገልጸዋል፡፡በዚህም በ2016 በጀት ዓመት 513 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ገልጸው÷ ይህም የዕቅዱን 96 በመቶ መሆኑን አንስተዋል።
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።