January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ጎንደር ከተማ ከእስራኤል እህት ከተሞች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ምክክር ተካሄደ

ጎንደር ከተማ እስራኤል ከሚገኙ እህት ከተሞች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ምክክር ተካሂዷል፡፡የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ ከእስራኤል ም/አምባሳደር ቶመር ባርላቪ ጋር በቱሪዝምና የእህትማማች ከተሞችን ማጠናከር በሚቻልብት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡ከዚህ ባለፈም የልማት እንቅስቃሴዎችን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡ምክክሩ ጎንደር ከተማ እስራኤል ካሉ እህት ከተሞች ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

FBC