January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት የ3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል ፍጻሜ ዛሬ ይካሄዳል

በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ የዛሬ መርሐ-ግብሮች ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍጻሜ እና የማጣሪያ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡በዚሁ መሠረት ምሽት 4 ሠዓት ከ43 ላይ በሚካሄደው 3 ሺህ ሜትር የወንዶች የፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ለሜቻ ግርማ፣ ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት ዋለ ይሳተፋሉ፡፡እንዲሁም ቀን 6 ሠዓት ከ10 ላይ በሚካሄደው 5 ሺህ ሜትር የወንዶች ማጣሪያ አትሌት ሐጎስ ገብረ ሕይወት፣ ቢንያም መሐሪ እና አዲሱ ይሁኔ ተሳታፊ ናቸው፡፡በሌላ በኩል እንዲሁም ትናንት በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ከምድቧ ያላለፈችው አትሌት ብርቄ ሓየሎም ዛሬ ቀን 7 ከ45 ላይ በድጋሚ በማጣሪያው የምትወዳደር ይሆናል፡፡በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምክ ኢትዮጵያ እስከ አሁን ሁለት የብር ሜዳሊዎችን በመያዝ 52ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡አሜሪካ፣ ቻይና፣ አውስትራሊያ እና ፈረንሳይ በቅደም ተከተል ከ 1 እስከ 4 ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

FBC