January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ 13 ተርባይኖች ተከላ ተጠናቀቀ

የአሰላ የንፋስ ኃይል በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሂጦሳ ወረዳ በኢተያ ከተማ አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከሚተከሉ 29 ተርባይኖች የ13ቱ ተከላ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ የሲቪል ሥራዎች ክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ ገለፁ፡፡ ባለሙያው አቶ ይድነቃቸው ደሳለኝ እንደገለፁት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈፃፀም 61 በመቶ ደርሷል። በፕሮጀክቱ ከሚተከሉት 29 የንፋስ ማማዎች ውስጥ የ23ቱ የመሰረት ሥራ የተጠናቀቀ ሲሆን አፈፃፀሙም 80 በመቶ መድረሱን ጠቁመዋል። 16 የንፋስ ማማዎችን ለመትከል የሚያስችሉ ዕቃዎች ከወደብ ተጓጉዘው ሳይት መድረሳቸውንም ነው አቶ ይድነቃቸው የገለፁት።

EBC