January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ለአረጋውያን እና በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች የሚደረገው የቤት ሥራ ላለፉት ስድስት ዓመታት በተግባር ላይ ይገኛል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ለአረጋውያን እና በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች የሚደረገው የቤት ሥራ እና የአዋሬ አካባቢ የለውጥ እንቅስቃሴ ላለፉት ስድስት ዓመታት በተግባር ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።የዘንድሮው የግንባታ ሂደት ፍጥነት እና ጥራት ላጣመረ የሥራ ባሕል ምሳሌ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። የቤት ግንባታ ብቻ ሳይሆን የአረንጓዴ ሥፍራዎቹ ግንባታ የጋራ እሳቤን እና ጉርብትናን የሚያዳብሩ፣ ለሰው ልጅ የሚገባውን የከበረ የአኗኗር ዘይቤ የሚያዳብሩ ናቸው ብለዋል።

EBC