ለ2017 በጀት ዓመት ከ550 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማፀደቅ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ፡፡የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ትግበራውን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ÷ የፖሊሲ ማሻሻያው ዘላቂና አስተማማኝ ኢኮኖሚ ለመገንባት መሠረት የሚጥል መሆኑን አስረድተዋል፡፡የፖሊሲ ማሻሻያው ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ የተለያዩ የፋይናንስ ምንጮች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ይህን ተከትሎ ገንዘብ ሚኒስቴር ለ2017 በጀት ዓመት ይፋ ካደረገው የፌዴራል መንግሥት በጀት ተጨማሪ በጀት እንደሚያፀድቅ አመላክተዋል፡፡ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማፀደቅ የተዘጋጀው ከ550 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑን ገልጸው÷ ከዚህ ወስጥ 240 ቢሊየኑ ለማኅበራዊ ልማት የሚውል ነው ብለዋል።መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲውን በተሟላ መልኩ ገቢራዊ ሲያደርግ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ታሳቢ በማድረግ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡በዚህም ቋሚ ገቢ ያላቸውና በልማታዊ ሴፍቲኔት ለሚታገዙ ዜጎች በቂ ድጎማ ለማድረግ ተጨማሪ በጀቱ ወሳኝ ሚና አለው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ተጨማሪ በጀቱ ለዘይት፣ ለነዳጅና ለመድኃኒት ድጎማ እንዲውል በማድረግ በፖሊሲው ትግበራ ጊዜ ሊደርሱ የሚችሉ ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከል እንደሚያስችልም ጠቅሰዋል፡፡ከዚህ ባለፈ ሀገራዊ ወጪን በራስ ገቢ ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የፖሊሲ ትግበራው የገቢ አቅምን በማሳደግ በኩል ወሳኝ ሚና እንዳለውም ነው ያነሱት፡፡
FBC
More Stories
የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ተገለጸ፡፡
የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተመረጡ የግብርና፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ እና ማዕድን ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበየቻይናዋ ግዛት ከፍተኛ ልዑካን የተሳተፉበት የቻይና-አፍሪካ (ኢትዮጵያ) የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝም ና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም ለ45ኛ በኢትዮጵያ ለ37ኛ በክልሉ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የዓለም የቱሪዝም ቀን ”ቱሪዝም ለሰላም” በሚል መር ቃል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነዉ።