በፓሪስ ኦሊምፒክ በማራቶን ኢትዮጵያን የሚወክለው አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለውድድሩ ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡አትሌት ቀነኒሳ በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳስታወቀው÷ ለፓሪሱ ኦሊምፒክ ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት አጠናቋል።በዝግጀቱ አብረውት ለነበሩት የቡድን አሰልጣኞች፣ ለቡድኑ አባላት፣ ለቤተሰቦቹ እና በመላው ዓለም ለሚገኙ አድናቂዎቹ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡እንደ ቡድን ጠንካራ ዝግጀት ማድረጋቸውን የገለፀው አትሌት ቀነኒሳ፤ ጠንካራ የቡድን ስሜት ለመፍጠር የሚያስችል የልምምድ ጊዜ ማሳለፍ መቻላቸውን ገልጿል።
FBC
More Stories
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል ከአስቶን ቪላ ጋር ይጫወታሉ
የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ኮከብ ማርሴሎ ጫማ ሰቀለ
አርሰናል ከካራባኦ ዋንጫ ተሰናበተ