በመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን በአጭር ጊዜ የማቋቋም ሥራ ይሰራል፣ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፥ የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤት በክልሉ የአደጋ ተጋላጭነት፣ ዝግጁነት እና ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ ውይይት አድርጓል።በክልሉ በመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን በአጭር ጊዜ የማቋቋም ሥራ በተቀናጀ መልኩ እንደሚከናወን የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገልጸዋል።በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የእለት ተደራሽ ሰብዓዊ ድጋፍ ከማቅረብ ባሻገር በአጭር ጊዜ የመኖሪያ ቤት በመስራት ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የጠቆሙት።በዘላቂነት አደጋን በራስ አቅም ለመቋቋም የመጠባበቂያ ክምችት እህል በስፋት መዘጋጀት እንዳለበት አቅጣጫ ያስቀመጡት ርዕሰ መስተዳድሩ ከዚህ ጋር ተያይዞ በወቅታዊ ችግር ወደ እርዳታ የገቡ ወገኖችን በዘላቂነት ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ማቅረብ አንገብጋቢ አጀንዳ በመሆኑ በየደረጃው መግባባት በመፍጠር ተግባሩን በትኩረት መስራት እንደሚገባ ያሳሰቡት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ በክልሉ ለሚከሰቱ አደጋዎች በአከባቢው ያሉ ሀብቶችን በማቀናጀት ፈጣን ምላሽ መሰጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።በክልሉ ለሚያጋጥሙ የአደጋ ክስተቶች ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ማቅረብ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አለመሆኑን የጠቆሙት የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፥ ኮሚሽነር ለማ መሰለ (ዶ/ር) ይህን ዕሳቤ እስከ ታቸኛው መዋቅር መግባባት በመፈጠር እንደሚገባ ገልጸዋል።በክልሉ የአደጋ ክስተት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና በዚህም በተለያየ ደረጃ የሚገለጽ ጉዳት መድረሱን የገለጹት ኮሚሽነሩ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት መዋቅር እና ህብረሰብን በማስተባበር የሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበላቸው መሆኑን ጠቁመዋል።በክልሉ የሚከሰቱ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋም በተሰጠው አቅጣጫ አንዳንድ የክልሉ ዞኖች ሀብት ማሰባሰብና ተጠባባቂ ምርት ማምረት መጀመራቸውን የገለጹት ኮሚሽነር ለማ (ዶ/ር) በአደጋው ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጹት።የክረምቱ ዝና እያየለ የሚሄድ በመሆኑ በክልሉ በ5 ዞኖች ውስጥ ባሉት 25 ወረዳዎች፣ በ184 ቀበሌዎች ናዳና ጎርፍ አደጋ ልከሰት እንደሚችል መተንበዩን የገለጹት ኮሚሽነር ለማ (ዶ/ር) በየመዋቅሩ የዝግጅቱ አቅም በማጠናከር አደጋዎች ስከሰቱ ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል።በተከናወኑ ክልላዋ የአደጋ ተጋላጭነት፣ የመከላከል፣ ክስተት እና ምላሽ ተግባራት ዙሪያ ኮሚሽነሩ ለማ መሰለ (ዶ/ር) የአፈፃፀም ሪፓርት ያቀረቡት ሲሆን የምክር ቤቱ አባላት ሀሳብ አስተያየት ሰጥተዋል።የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው በየመዋቅሩ ግብረሃይል በማቋቋም ተጋላጭነትና ክስተት በተገቢው በመለየት ምላሽ የመስጠት ስራ እየተሰራ እንደሆነና በዘላቂነት ከማቋቋም አኳያ የመሬት ልየታ እና ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።የዘገበው የክልሉ መ/ኮ/ጉ/ቢሮ ነው ።
Woreda to World
More Stories
የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)