የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በሸካ ዞን፥ ግንባታው እየተፋጠነ ያለውን የማሻ ሳብስቴሽን የከፍተኛ ኃይል መስመር ዝርጋታ የስራ እንቅስቃሴ፣ የጎሬ-ማሻ ቴፒ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ እንዲሁም ጭነጋዋ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን ጎብኝተዋል።
የጎሬ-ማሻ ቴፒ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታው ስጠናቀቅ ከሚያስገኘው የኢኮኖሚ ፋይዳ ባሻገር አከባቢው ለኢኮ-ቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ በመሆኑ ተጨማሪ ውቤትን የሚያግናጽፍ መሆኑ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት።
የሳብስቴሽን ግንባታ ተጠናቆ ለህብረተሰቡ ተገቢውን ግልጋሎት እንዲሰጥ የአከባቢው መንግሥት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ያሳሰቡት ርዕሰ መስተዳድሩ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአግልግሎት እንዲበቃ የክልሉ መንግሥት ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የመቱ-ማሻ ስባስቴሽን ስራአስኪያጅ እንጂነር ጌታቸው አሳዬ እንደገለጹት የማከፋፈያ ጣቢያ ሀይል ተሸካሚ ምሶሶ ተከላ ስራን ለማጠናቀቅ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነና አጠቃላይ የሳብስቴሽን ግንባታ 80 ከመቶ መጠናቀቁን ተናግረዋል።
ሳብስቴሽን ግንባታውን የሚያከናውነው የሲኖ ሀይድሮ ቻይና ካምፓኒ እንደሆነና ቀሪ ስራዎችን እስከ ታህሳስ ባለው ጊዜ በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ሀይል ለማቅረብ እንደሚሰራ ነው የተገለጸው።
More Stories
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ልዩ የአዳር ትምህርት ተመቻችቶ የመማር ማስተማር ስራ መጀመሩ የበለጠ ውጤት እንድናስመዘግብ አግዞናል ሲሉ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ልዩ የአዳር ትምህርት እድል ያገኙ ተማሪዎች ገለፁ ።