ግንባታው በቀድሞው የደቡብ ክልል ጊዜ በ2004 ተጀምሮ የተቋረጠውና ከክልሉ ምሥረታ ጀምሮ በአዲስ መልክ ወደ ግንባታ የተገባው በሸካ ዞን፥ አንድራቻ ወረዳ የጌጫ-ሸኪበዶ የገጠር መንገድ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለአግልግሎት መብቃቱ ትልቅ ደስታን እንደፈጠረባቸው ነው ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የገለጹት።ከዚህ በፊት የመንገድ መሠረተ ልማት በአከባቢው ባለመኖሩ ወላድ እናቶችን ወደ ጤና ተቋም ለማድረስ እንዲሁም የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ አዳጋች እንደነበረ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ ከከልሉ ምሥረታ ወዲህ ይህን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመፍታት ለተሰጠው ትኩረት የክልሉ መንግሥትን አመስግነዋል።በአከባቢው በቡና ልማት ኢንቨስትመንት የተሰማራው የዱባዩ ሉታ ኢንዱስትሪ ጉሩፕ ስራ አስፈፃሚ መሀመድ ሰሀላ (ዶ/ር) እንደገለጹት የመንገዱ ግንባታ መጠናቀቅ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ከቦታ ቦታ ለማጓጓዝ ትልቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።ስራ አስፈፃሚው አክለው ድርጅታቸው በአከባቢው የመንገድ ግንባታውን ጨምሮ በሌሎችም ማህበራዊ አግልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንባታ ድጋፍ ማድረጉን በመገልጽ በዚህም የተጣለባቸውን ማህበራዊ ኃላፊነት በብቃት እየተወጡ መሆኑን ጠቁመዋል።27 ኪሎሜትር የሚረዝመውና አራት አጎራባች ቀበሌዎችን የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታው በክልሉ መንግሥት 30 ሚሊዮን ብር በጀት ተገንብተው ለአግልግሎት ከፍት መሆኑ የሚታወስ ነው።
Woreda to World
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።