January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮች እና ሠራተኞች በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶው አየር መንገድ ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ የአካባቢ ጥበቃን እንደ አንድ ማኅበራዊ ኃላፊነት ይዞ እየሠራ መሆኑን አስታውቀው፣ ከችግኝ ተከላ በተጨማሪም ለአካባቢ ምቹ እና ተስማሚ የሆኑ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ በማዋል የራሱን አስተዋፅዖ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። አየር መንገዱ አዳዲስ እና ዘመናዊ አውሮፕላኖችን የበረራ አገልግሎት ላይ በማዋል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ በአየር መንገዶች በሚደረገው ርብርብ አካል በመሆን እየሠራ ነው ብለዋል፡፡