November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታ የህብረተሰቡ ተሳትፎ መጠናከር ይገባል፦ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

በክልሉ በስፋት የሚነሳውን የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄ በመንግሥት አቅም ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ የህብረተሰቢ እና የሌሎች የልማት አጋሮች ተሳትፎ መጠናከር እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ጠይቀዋል።ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ሸካ ዞን፥ አንድራቻ ወረዳ የተገነባውንና 4 ቀበሌዎችን የሚያገናኘውን የጌጫ -ሸኪበዶ ገጠር መንገድ ፕሮጀክት መርቀው ከፍተዋል።ክልሉ ከተደራጀህ ወዲህ ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ አግልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የክልሉ መንግሥት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ከነዚህም አንዱ ዛሬ ግንባታው ተጠናቆ ለምረቃ የበቃው የጌጫ -ሸኪበዶ ገጠር መሆኑን ጠቁመዋል።ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ በመፍታት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።የተገነባው መንግድ አውታር ተገቢውን አግልግሎት እንዲሰጥ ተጠቃሚው ህብረተሰብ የመንግዱን ደህነት መጠበቅ እንዳለበት ያስገነዘቡት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ ለመንገዱ ደህነት አስፈላጊውን ክትትልና ጥገና ተቋማቸው እንደሚያከናውን ተናግረዋል።የመንገዱ ግንባታ ስራው ሙሉ በሙሉ በራስ አቅም በክልሉ መንገዶች ባለስልጣን መከናወኑን የገለጹት የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ዳይሬክተር እንጂነር አብድዩ መኮንን ለዚሁም የ30 ሚሊዮን ብር በጀት ድጎማ በክልሉ መንግሥት መደረጉን አስታውቀዋል።ለፕሮጀክቱ መጠናቀቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን ያመሰገኑት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ መንገዱ ለአግልግሎት መብቃቱ ከአከባቢው ለገበያ የሚወጣውን የግብርና ምርቶች በቀላሉ ተደራሽ በማድረግ የአከባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።የመንገድ መሠረተ ልማት ለአንድ አከባቢ ሁለንተናዊ ዕድገት የጎላ ድርሻ እንዳለው የገለጹት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ የጌጫ -ሸኪበዶ ገጠር መንገድ የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እንደነበረ አውስተዋል።ከዚህ በፊት በመንግድ እጦት የአከባቢው ማህበረሰብ ለተለያዩ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ስዳርግ መቆየቱን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው አሁን ላይ የመንገዱ መጠናቀቅ ለአከባቢው ትልቅ እፎይታን የሚሰጥ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።