November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡን በቁንጽል ሳይሆን በምልዐት መመልከት ይገባል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡን በቁንጽል ሳይሆን በምልዐት መመልከት ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት፥ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡን በቁንጽል ሳይሆን በምልዐት መመልከት ይገባል። በመደመር ዕሳቤያችን ለሀገር ልማት ምን መደረግ እንዳለበት በጥልቀት መዝነን አስቀምጠናል ያሉ ሲሆን፥ ዓላማችን የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡አካሄዳችን ድሃ ተኮር፤ ትኩረታችን ለችግር በመጠቃት ተጋላጭ የሆኑ ደካሞችን መደገፍ ነው ሲሉም ነው የገለጹት። የለውጥ ሥራዎቻችን ሁሉ ስኬት በባለድርሻ አካላት የተባበረ ጥረት ላይ ይመሠረታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ይህም ምርታማነትን፣ የውጭ ንግድንና ገቢን ተባብሮ ማሳደግ ማለት እንደሆነ አንስተዋል፡፡የሕግ አስፈጻሚ አካላት የለውጥ ሥራውን ባልተገባ ሕገ-ወጥ መንገድ ለመጠቀም በሚፈልጉ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ኃላፊነት እንደተሰጣቸውም ነው የገለጹት። እነዚህን ሃሳቦችም ዛሬ ጠዋት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በነበራቸው መድረክ መግለጻቸውን ጠቅሰው፥ የበለጠ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የመድረኩን ውይይት በሚዲያዎች መከታተል እንደሚቻል አመላክተዋል።

FBC