January 28, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በፓሪስ ኦሎምፒክ ተጠባቂ የአትሌቲክስ ውድድሮች መካሄድ ጀምረዋል

ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ መድረክ 58 ሜዳልያዎችን አግኝታለችየፓሪስ ኦሎምፒክ ስድስተኛ ቀኑን ሲይዝ የአትሌቲክስ ውድድሮች ተጀምረዋል።ጠዋት ላይ የ20 ኪሎሜትር እርምጃ ውድድር ሲካሄድ ኢኳዶራዊው አትሌት ብሪያን ፒንታዶ አሸናፊ ሆኗል።የ29 አመቱ አትሌት ውድድሩን ለማጠናቀቅ 1 ሰአት ከ18 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ፈጅቶበታል።የብራዚሉ ካዬ ቦንፊም እና ስፔናዊዎ የአለም ሻምፒዮን አልቫሮ ማርቲን የብር እና የነሀስ ሜዳልያ አግኝተዋል።ኢትዮጵያዊው ምስጋና ዋኩማ ደግሞ ስድስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።የፓሪስ ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ውድድሮች ሲቀጥሉ ምሽት 4 ስአት ከ20 ላይ የሚደረገው የወንዶች 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ይጠበቃል።የቶኪዮ ኦሎምፒክ አሸናፊው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በምሽቱ ውድድር የማሸነፍ ግምት ተሰጥቶታል።ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች የሚሳተፉባቸው የማጣሪያ እና ግማሽ ፍፃሜ ውድድሮች ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄዱ ሲሆን፥ ሰኞ ምሽት 4 ሰአት ከ10 የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ይደረጋል።ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው የፍፃሜ  ውድድሮች መርሀግብርሀምሌ 29 2016ምሽት 4 ሰአት ከ10- 5 ሺህ ሜትር ፍፃሜ (ሴቶች)ምሽት 4 ሰአት ከ45- 800 ሜትር ፍፃሜ (ሴቶች)ሀምሌ 30 2016ምሽት 3 ሰአት ከ50 – 1500 ሜትር ፍፃሜ (ወንዶች)4 ሰአት ከ10 – 3000 ሜትር መሰናክል ፍፃሜ (ሴቶች)ነሀሴ 1 2016ምሽት 4 ሰአት ከ40- 3000 ሜትር መሰናክል ፍፃሜ (ወንዶች)ነሀሴ 3 2016ምሽት 3 ሰአት ከ55- 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ (ሴቶች)ነሀሴ 4 2016ጠዋት 3 ሰአት- ወንዶች ማራቶን ፍፃሜምሽት 3 ሰአት- ወንዶች 5 ሺህ ሜትር ፍፃሜምሽት 3 ሰአት ከ25- 1500 ሜትር ሴቶች ፍፃሜነሀሴ 5 2016ጠዋት 3 ሰአት- ሴቶች ማራቶን ፍፃሜ በ1956 በሜልቦርን ኦሎምፒክ ተሳትፎዋን አሀዱ ያለችው ኢትዮጵያ በታሪካዊው መድረክ 58 ሜዳልያዎችን አግኝታለች።  ያገኘቻቸው 23 የወርቅ፣ 12 የብር እና 23 የነሀስ ሜዳልያዎች ሁሉም በአትሌቲክስ ውድድሮች የተገኙ ሲሆን 11 አትሌቶች ከአንድ በላይ የኦሎምፒክ ሜዳልያ አግኝተዋል።በፓሪስ ኦሎምፒክስ ምን ያህል ሰኬታማ ትሆናለች የሚለው ከዛሬ ምሽቱ የ10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድ ጀምሮ የሚታይ ይሆናል።

Al Ain