October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ ተጥሎ የቆየው የባንክ የውጭ ምንዛሪ ገደብ ተሻረ

ሙሉ በሙሉ በነዳጅ የሚሰሩ በታሪፍ መፅሐፉ አንቀፅ 87.03 የሚመደቡ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ዕገዳ እንደተጠበቀ ሆኖ በተቀሩት ዕቃዎች ላይ የተጣለው የውጭ ምንዛሪ ገደብ ውሳኔ ከነማሻሻያው የተሻረ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።መንግሥት በቁጥር ክሂገ 1/7/252 በቀን 04/02/2015 በተላለፈ ውሳኔ እና በቁጥር ታፖመ/ፖ/29/16 በቀን 28/6/2016 በተሻሻለው መሰረት በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የባንክ የውጭ ምንዛሪ ገደብ እንዲጣል ማድረጉ ይታወሳል።አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ በነዳጅ የሚሰሩ በታሪፍ መፅሐፉ አንቀፅ 87.03 የሚመደቡ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እገዳ እንደተጠበቀ ሆኖ በተቀሩት ዕቃዎች ላይ የተጣለው የውጭ ምንዛሪ ገደብ ውሳኔ ከነማሻሻያው ከሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የተሻረ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

EBC