በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሙያ የሆኑት አቶ አዳነ ቆጭቶ በክልሉ ካፋ እና ሸካ ዞኖች ህገወጥ የመድኃኒት ክትትልና ቁጥጥር ስራዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል።በካፋ ዞን ብቻ በ5 ወረዳዎች በ46 የግል ጤና ተቋማት ላይ በተደረገው አሰሳ ግምታዊ ዋጋቸው 2.6 ሚሊዮን የሚያወጡ ህገወጥ መድኃኒቶች ተገኝተው ርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል።ህገወጥ የመድኃኒት ዝውውር በክልሉ ስጋት ሆኗል ያሉት አቶ አዳነ የተጠናከረ የቅንጅት ስራ በመስራት ምሽቱን በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ግምታዊ ዋጋቸው ህገወጥ መድኃኒት 641,630 ሺህ ብር የሚያወጡ 44 ዓይነት የተለያዩ መድኃኒቶች ከሌሊቱ 6:00 አካባቢ በቁጥጥር ስር በማዋል ህጋዊ ርምጃ ለመውሰድ ክስ መመስረቱን አስረድተዋል።መነሻውን ከጂማ አድርጎ ወደ ሸይቤንች ወረዳ ሲጓዝ የነበረው ይህ መኪና በጥርጣሬ ሲያዝ ከሸቀጣሸቀጥ ጋር ህገወጥ መድኃኒት ጭኖ ለማምለጥ በመሞከሩ ፖሊስ ተከታትሎ መያዙን የቦንጋ ከተማ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ዋና ሳጂን አገኘሁ ማሪቶ ተናግረዋል ።ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ መድኃኒት በህብረተሰቡ ላይ የጤና ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ ህብረተሰቡ ህገወጥነትን ከጸጥታው አካላት ጋር መሆን እንዲተባበር የጠየቁት የካፋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አክሊሉ አሰፋ ናቸው ።በቦንጋ ከተማ የተያዘው ህገወጥ የመድኃኒት ዝውውር ከመኪና ቅባቶችና ከሌሎች የፋብሪካ ውጤቶች ጋር መሆኑ ከፈዋሽነቱ ይልቅ መርዛማ የመሆን ዕድሉ ሰፊ በመሆኑ ህብረተሰቡ የህግ ውሳኔ ሲያገኝ ይወገዳል ሲሉም ተናግረዋል ።የጤና ባለሙያዎች የህሊና ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ ህብረተሰቡን ሊጎዱ ከሚችሉ አሰራሮች ሊቆጠቡ እንደሚገባ አቶ አክሊሉ አሳስበዋል ።በዞኑ በተደረገው የተጠናከረ የቁጥጥርና የክትትል ስራዎች በ46 የግል ጤና ተቋማት ችግር በታዩባቸው 23 የግል ጤና ተቋማት ላይ ርምጃ መወሰዱንም አብራርተዋል ።የዘገበው የክልሉ መ/ኮ/ጉ/ቢሮ ነው
Woreda to World
More Stories
የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ተገለጸ፡፡
የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተመረጡ የግብርና፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ እና ማዕድን ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበየቻይናዋ ግዛት ከፍተኛ ልዑካን የተሳተፉበት የቻይና-አፍሪካ (ኢትዮጵያ) የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝም ና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም ለ45ኛ በኢትዮጵያ ለ37ኛ በክልሉ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የዓለም የቱሪዝም ቀን ”ቱሪዝም ለሰላም” በሚል መር ቃል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነዉ።