January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሩሲያ አብዛኞቹን የጦር መርከቦቿን ያካተተ ልምምድ ጀመረች

ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረች ወዲህ ብቻዋን እና ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ከአጋሮቿ ጋር በመሆን ብዙ ወታደራዊ ልምምዶችን አካሂዳለች

ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ልምምዱ የጸረ-አውሮፕላን ሚሳይል፣ ከባድ መሳሪያ፣ የጸረ-ባህር ሰርጓጅ መርከብ መሳሪያ አጠቃቀም ጨምሮ 300 የውጊያ ልምምዶችን ያካትታል

ሩሲያ አብዛኞቹን የጦር መርከቦቿን ያካተተ ልምምድ ጀመረችሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረች ወዲህ ብቻዋን እና ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ከአጋሮቿ ጋር በመሆን ብዙ ወታደራዊ ልምምዶችን አካሂዳለች

የሩሲያ ባህር ኃይልሚኒስቴሩ እንደገለጸው ልምምዱ የጸረ-አውሮፕላን ሚሳይል፣ ከባድ መሳሪያ፣ የጸረ-ባህር ሰርጓጅ መርከብ መሳሪያ አጠቃቀም ጨምሮ 300 የውጊያ ልምምዶችን ያካትታልሩሲያ አብዛኞቹን የጦር መርከቦቿን ያካተተ ልምምድ ጀመረች።ሩሲያ ባህር ኃይል አብዛኞቹን የጦር መርከቦቿን በመጠቀም በአርክቲክ፣ በፓሲፊክ እንዲሁም በባልቲክ እና በካስፒያን ባህሮች ልምምድ ማድረግ መጀመሯን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዛሬው እለት አስታውቋል።ወታደራዊ ተንታኞች ሩሲያ በዓለም በጠንካራ የባህር ኃይል ከአሜሪካ እና ከቻይና ቀጥሎ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጧታል። ሩሲያ በቂ የሚባል ኑክሌር ተሸካሚ ባህር ሰርጓጅ መርከቦችም ባለቤት ነች። 20ሺ ወታደሮች እና 300 መርከቦችን የሚያካትተው የሩሲያ ልምምድ የባህር ኃይሉን ዝግጁነት እና አቅም በሁሉም ደረጃ ለመላካት እንደሚጠቅም ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል። ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ልምምዱ የጸረ-አውሮፕላን ሚሳይል፣ ከባድ መሳሪያ፣ የጸረ-ባህር ሰርጓጅ መርከብ መሳሪያ አጠቃቀም ጨምሮ 300 የውጊያ ልምምዶችን ያካትታል።”የሩሲያ ባህር ኃይል የተለያዩ አደረጃጀቶች በሰሜን የልምምድ ቀጣናዎች፣ በፓሲፊክ እና በባልቲክ እንዲሁም በካስፒያን ባህር በታቀደው መሰረት ለምምድ ማካሄድ ጀምረዋል” ብሏል ሚኒስቴሩ።ሚኒስቴሩ እንደገለፈጸው በዚህ ልምምድ 300 መርከቦች እና ጀልባዎች፣ ሰርጓጆች እና ደጋፊ መርከቦች፣ 50 የጦር ጀቶች እና ከ200 በላይ ወታደራዊ ቡድኖች እና ልዩ መሳሪያዎች በልምምዱ ይካተታሉ።በጥቁር ባህር ያለው የሩሲያ የባህር ኃይል ጦር ፕሬዝደንት ፑቲን በሺዎች የሚቆጠር ጦር ወደ ዩክሬን ከላኩ ጀምሮ በልምምዶች ላይ ተሳትፎ አያውቅም።ፕሬዝደንት ፑቲን የሩሲያ የባህር ኃይል ቀን ባለፈው ቅዳሜ እለት በተከበረበት ወቅት ዋሸንግተን ወደ ጀርመን የረጅም ርቀት ሚሳይል የምትልክ ከሆነ ሩሲያም ምዕራባውያንን ለመምታት በሚያስችል ርቀት ላይ ሚሳይል እንደምታስቀምጥ አሜሪካን አስጠንቅቀዋል።ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረች ወዲህ ብቻዋን እና ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ከአጋሮቿ ጋር በመሆን ብዙ ወታደራዊ ልምምዶችን አካሂዳለች።

Al Ain