January 28, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ለብቻ የመቆም ማሳያ፥ ከግርሻውያን ኀልዮት የማፈንገጫ፤ የእውነት አምድ፥ የጽናት ጉልላት … አቡነ ጴጥሮስ።

“ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” በተሰኘው፥ በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን ቲያትር ላይ፥ ግርሻ የተሰኘ የዘመኑን አጎብዳጆች እሚወክል ገጸባህርይ አለ። “ለጥልያን እጅ እንስጥ” እሚልበት አመክንዮ የዋዛ እሚባል አይደለም። ለአቡነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያን ፍጹም ሞት እሚያትትበት መንገድ አጀብ ነው። በቃላት አሽሞንሙኖ “ኢትዮጵያ ሞታለች” ብሎ ሊያረዳቸው ይባትላል። አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያን ከድተው በፋሽስት እንዲጠመቁ ሲያብል። አቡኑም እንዲህ ይሉታል፦ “እኔ በኢትዮጵያ ስለማምን፥ እኔ እስካመንኩ እሷ አትሞትም።”

አቡነ ጴጥሮስ የዛሬ 88 ዓመት ነበር ሰማዕትነትን የተቀበሉት!