January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ትራምፕ ምርጫውን ካሸነፉ ወዲያውኑ ሩሲያ እና ዩክሬንን ወደማደራደር መግባት እንደሚፈልጉ ኦርባን ተናገሩ

አርባን ትራምፕ ዩክሬን እና ሩሲያን ማደራደር እንደሚፈልጉ ለአውሮፓ መሪዎች የተናገሩት በዋሽንግተን ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ነውትራምፕ ምርጫውን ካሸነፉ ወዲያውኑ ሩሲያ እና ዩክሬንን  ወደማደራደር እንደሚገቡ ኦርባን ለአውሮፓ ህብረት በጻፉት ደብዳቤ ገልጸዋል።የሪፐብሊካኑ እጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በመጭው ህዳር የሚካሄደውን ምርጫ የሚያሸንፉ ከሆነ ሩሲያ እና ዩክሬንን ወዲያውኑ ወደማደራደር እንደሚገቡ የሀንጋሪው ጠቅላይ  ሚኒስትር ቪክተር ኦርባን በጽሁፍ ለአውሮፓ መሪዎች ነግረዋቸዋል ተብሏል።ለአውሮፓ ህብረት ካውንስል ምክርቤት ፕሬዝደንት ቻርለስ ሚሸል እና ለሁሉም መሪዎች የተጋራው ይህ ደብዳቤ የተጻፈው፣ ኦርባን ከትራምፕ ጋር ካወሩ እና እንዲሁም ዩክሬንን፣ ሩሲያን እና ቻይናን ከጎበኙ በኋላ ነው።

Al-Ain