ሰራዊቱ ከሚሰጠው ሀገራዊ ግዳጅ በተጨማሪ መሰል ሀገራዊ እንቅስቃሴ ላይ አሻራውን እንደሚያሳርፍ እና በሀገሪቱ የልማት ተሳትፎ ላይ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለፁ። የኢፌዴሪ አየር ኃይል በዛሬው እለት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እያከናወነ ይገኛል። በዚህ ወቅት የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ ሰራዊቱ በሀገሪቱ የልማት ተሳትፎ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በተለይም በአረንጓዴ አሻራ ሰፊ ስራ እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። የሚተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ረገድ አየር ኃይሉ በትኩረት ይሰራል ያሉት ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ ሰራዊቱ ከሚሰጠው ሀገራዊ ግዳጅ በተጨማሪ መሰል ሀገራዊ እንቅስቃሴ ላይ አሻራውን ያሳርፋል ብለዋል። አየር ኃይሉ እንደተቋም በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 25 ሺ ችግኞችን ለመትከል እንደሚሰራ የተገለፀ ሲሆን፤ በዛሬው መርሃ ግብር 10 ሺህ የቡና ችግኞች ጨምሮ የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች እየተተከሉ እንደሚገኝ ተጠቅሷል።
EBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።