“የምትተክል አገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አካል እንደሆነም በወቅቱ ተጠቁሟል።በቦታው ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደምሴ ደንቦ እንደተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ስራ የዜግነት ግዴታ እየሆነ የመጣ ከመሆኑም በላይ የሁሉም ህብረተሰብ ግንዛቤ እያደገ መጥቷል ብለዋል።የሸካ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ በላቸው ጋራ በበኩላቸው የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎችን በግቢው በሚኖራችሁ ቆይታ ሁሉ የዞኑ መንግስትም ሆነ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግና አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ተሳታፊ በመሆናችሁ ልትኮሩ ይገባችኋል ብለዋል።በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ዋና ስራ አስፈፃሚ መንግስቱ ከተማ ባስተላለፉት መልዕክት የዘንድሮ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቤታችሁ አሻራችሁን በማኖራችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለው በፈተናው ውጤታማ እንዲሆኑም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።በግቢው ቆይታችሁ ደስተኛ እንዲትሆኑ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ተፈታኞች ያለምንም ስጋት ፈተናው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።በመርሃግብሩ ላይ የግቢው መምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች፣የክልል፣የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የዘንድሮ አገር አቀፍ 12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል የዘገበው የዞኑ መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤ/ት ነው ።
Woreda to World
More Stories
የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)