እጩ ፕሬዝዳንቱ ንግግር በማድረግ ላይ ሳሉ የጥይት ድምጽ ከተሰማ በኋላ ጆሯቸው አካባቢ ደምተው ታይተዋልዶናልድ ትራምፕ የግድያ ሙከራ ተፈጸመባቸው።በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል።የፊታችን ህዳር ወር ላይ በሚካሄደው ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩት ዶናልድ ትራምፕ የየምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ቆስለው ወደ ህክምና ተወስደዋል።ቪኦኤ እንደዘገበው ከሆነ ዶናልድ ትራምፕ በፔንሲልቫኒያ ግዛት ለደጋፊዎቻቸው ንግግር በማድረግ ላይ ሳሉ የጥይት ድምጽ ተሰምቷል።ወዲያውኑም ትራምፕ ጆሯቸው አካባቢ ደም የታየባቸው ሲሆን የደህንነት ሰዎች እጩ ፕሬዝዳንቱን ወደ ተሽከርካሪ ውስጥ በማስገባት ከተጨማሪ ጉዳቶች እንደታደጓቸው ተገልጿል።የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን እንዳሳወቀው ትራምፕ አነስተኛ የመቁሰል አደጋ ከማጋጠሙ ውጪ ደህና መሆናቸውን ተናግሯል።ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ሚስጢራዊ ደህንነት ባለሙያዎችን ጥረት አመስግነዋል የተባለ ሲሆን ልጃቸው ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየር በኤክስ አካውንቱ “አሜሪካንን ለመጠበቅ መዋጋቱን አያቆምም” ሲል አጋርቷል።ታዋቂ የአሜሪካ ፖለቲከኞች የግድያ ሙከራውን በማውገዝ ላይ ሲሆኑ የሀገሪቱ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራዎችን በማካሄድ ላይ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።ፕሬዝዳንት ባይደን በዶናልድ ትራምፕ ላይ ስለተፈጸመው ክስተት ማዘናቸውን ገልጸው “ትራምፕ ደህና መሆኑ መልካም ነው፣ እንዲህ አይነት ህግወጥነት በአሜሪካ ቦታ የለውም” ሲሉ የግድያ ሙከራውን አውግዘዋል።ዘግይተው ይፋ በሆኑ ዘገባዎች መሰረት የግድያ ሙከራውንን የፈጸመውን ግለሰብ ጨምሮ ሌላ አንድ ሰው እንደተገደሉ ተገልጿል።
Al-Ain
More Stories
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ
አስደንጋጩ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት አልበረደም