ፖርቹጋላዊው እግር ኳስ ተጫዋች ሊዊስ ናኒና ናይጄሪያዊው እግር ኳስ ተጫዋች ኑዋንኩ ካኑ በኢትዮጵያ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች ስኬታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን አሉ። ፖርቹጋላዊው እግር ኳስ ተጫዋች ሊዊስ ናኒና ናይጄሪያዊው እግር ኳስ ተጫዋች ኑዋንኩ ካኑ ዛሬ ማለዳ ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል። ተጫዋቾቹ አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ደኤታ ስለሺ ግርማ፣ የመቻል ስፖርት ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሰይፈ ጌታሁን፣ የመከላከያ ሚዲያ ሥራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ኩማ ሚደቅሳ እንዲሁም የመቻል ስፖርት ክለብ ቴክኒካል ዳይሬክተር ኢኒስትራክተር አብርሃም መብራቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ተጫዋቾቹ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የመቻል 80ኛ የዓመት ምስረታ በዓል ላይ እንዲገኙ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ነው። ፖርቹጋላዊው እግር ኳስ ተጫዋች ሊዊስ ናኒ፤ ኢትዮጵያ በመምጣቴ በጣም ደስተኛ ነኝ ብሏል።
EBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።