በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከታክስ ዕዳ ከ49 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከታክስ ዕዳ 41 ቢሊየን 662 ሚሊየን 896 ሺህ 213 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 49 ቢሊየን 664 ሚሊየን 299 ሺህ 370 ብር መሰብሰቡን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ከፍተኛ የታክስ ዕዳ መጠን ያለባቸውን ታክስ ከፋዮች በመለየት ቅድሚያ ተሰጥቶ መሠራቱና ለዋና መስሪያ ቤት በልዩ ሁኔታ እንዲታዩ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ፈጥኖ ምላሽ መስጠቱ ለዕቅዱ መሳካት ማገዙ ተገልጿል፡፡
ከተሰበሰበው የታክስ ዕዳ ውስጥ 30 ቢሊየኑ 30 ቀን ካልሞላው የታክስ ዕዳ መሰብሰቡን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።