October 5, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን በመከላከል በተመድ እውቅና አገኘች

 ኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን ለመከላከል በሰራችው ውጤታማ ሥራ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ሥነ ሕዝብ ድርጅት እውቅና አገኘች።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በትናንትናው እለት በኒውዮርክ የተመድ ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ የኢትዮጵያ መንግስት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ የወሰዳቸውን የህግ፣ የፖሊሲና የፕሮግራም እርምጃዎች አብራርተዋል።

እውቅናና ሽልማቱ መንግስት ለስርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት የበለጠ የሚያጠናክር እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሃመድ፣ የተመድ ሥነ ህዝብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ናታኒያ ካኔምና ሌሎች የተመድ አባል ሀገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስወገድ የተቋቋመው ጥምረት በፈረንጆቹ 2012 የተመሰረተ ሲሆን÷ በጥምረቱ ውስጥ የመንግስት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የምርምር ተቋማትና የሃይማኖት ተቋማት ይገኛሉ፡፡

FBC