በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ ሩሲያ ገብቷል፡፡
ልዑኩ ለብሪክስ አባል ሀገራት በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ በተዘጋጀው ፓርላሜንታዊ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ነው ሩሲያ የገባው፡፡
ጉባዔው ሐምሌ 4 እና 5 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን÷በዛሬው ዕለት የብሪክስ አባል ሀገራት በተለያዩ የባለ ብዙ ወገን የግንኙነት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተጠቅሳል፡፡
በጉባዔው የአባል ሀገራቱን ትብብር እና ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚረዳ ፕሮቶኮል እና በጋራ ለመሥራት የሚረዳ ስምምነትም መፈረሙ ተጠቁሟል፡፡
በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያን ፓርላማ አቋም እና የግንኙነት ዝግጁነትን በተመለከተ በአፋ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጻ መደረጉን የፌደሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ የፓርላሜንታዊ ዲፕሎማሲ፣ ቀጣይነት ያለው እድገት፣ ዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ትኩረት የሰጡባቸው ነጥቦች ናቸው ተብሏል፡፡
አፈ-ጉባዔ አገኘሁ በዚሁ ወቅት÷ የኢትዮጵያ ፓርላማ የተሳታፊነት ብቻ ሳይሆን የመሪነት ሚናውን ጭምር በብቃት እንደሚወጣ አመላክተዋል፡፡
መድረኩ በሁለት ቀናት ውሎው በእነዚህና በሌሎች ርዕሳነ ጉዳዮች ላይ መክሮ ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
FBC
More Stories
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ልዩ የአዳር ትምህርት ተመቻችቶ የመማር ማስተማር ስራ መጀመሩ የበለጠ ውጤት እንድናስመዘግብ አግዞናል ሲሉ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ልዩ የአዳር ትምህርት እድል ያገኙ ተማሪዎች ገለፁ ።